የአካባቢ መሪዎች አባላት ቅዱስ ቁርባንን ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ለመወሰን ይመክራሉ፡፡
የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቀዳሚ አመራር እና የአስራሁለቱ ሃዋርያት ጉባኤ አባላት በአለም ለሚገኙ የቤተክርስቲያን አባላት መጋቢት 12 ቀን 2020 የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዉድ ወንድሞች እና እህቶች
በመጋቢት 11 ቀን 2020 ደብዳቤያችን ቃል እንደገባነው በአለም ዙሪያ ያለውን የCOVID-19 (የኮሮና ቫይረስ)ን የተመለከቱ ለውጦችን መከታተላችንን እንቀጥላለን፡፡ የቤተክርስቲያን መሪዎችን፣የመንግስት ባለስልጣናትን እና የህክምና ባለሙያዎችን ምክሮች ከግምት አስገብተናል እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ የጌታን መመሪያ ጠይቀናል፡፡ በመሆኑም የሚከተለውን ወቅታዊ የሆነ አቅጣጫ አስቀምጠናል፡፡
ከአሁን ሰኣት ጀምሮ ላልተወሰኑ ጊዚያት የቤተክርስቲያን አባላት ማንኛውም ህዝባዊ ስብሰባዎች ሌላ ማብራሪያ እስከሚሰጥ ድረስ በአለም ዙሪያ ታግዷል፡፡ ይህም የሚከተሉትን ይጨምራል፡፡
- የካስማ ስብሰባዎች፣የመሪዎች ስብሰባዎች እና ሌሎች ትልልቅ ስብሰባዎች
- የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎችን ጨምሮ ሁሉም ህዝባዊ የአምልኮ አገልግሎቶች
- የቅርንጫፍ፣የአጥቢያ እና የካስማ አክቲቪቲዎች
የሚቻል በሚሆንበት ጊዜ እባካችሁ አስፈላጊ የሆኑ የመሪዎች ስብሰባዎችን በቴክኖሎጂ አማካኝነት ማድረግ፡፡ የተለዩ ጥያቄዎች ቢኖሩ ወደ የአካባቢ የክህነት መሪዎች ሊላኩ ይችላሉ፡፡ ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ ተጨማሪ መመሪያዎች ወደፊት ይሰጣሉ፡፡
ኤጲስ ቆጶሳት ቅዱስ ቁርባንን ለአባላት ቢያንስ በወር አንዴ እንዴት ማድረስ እንደሚቻል ለመወሰን ከካስማ መሪዎች ጋር መመካከር አለባቸው፡፡
በአገልግሎት ጥረታቸው አንዳቸው ላንዳቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አባላትን እናበረታታለን፡፡ ሌሎችን ለመባረክ እና ከፍ ለማድረግ የአዳኙን ምሳሌ መከተል ይኖርብናል፡፡
ከሠላምታ ጋር
ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ አባላት